በ2014ዓ.ም ህዳር 6 በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ማኅበራት ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 985/2009 ዓ.ም አንቀጽ 10 መሠረት ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብደር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኅብረት ሥራ ማኅበር በህግ ታዉቆ በመዝገብ ቁጥር አራ/1/1/750/2014 ዓ.ም የተመዘገበ ነው፡፡
ቤትጎኅ ማለት የማለዳ ጀንበር፣ ንጋት፣ ብስራት ነው፡፡ አንድ ሀገር የኢኮኖሚ ዋልታዋን ለማጽናት ቁጠባን ባህል ያደርጉ ህዝቦች ሲኖሯት ነው፡፡ የሀገሪቷ ህብረተሰብ እንደ ግልም ሆነ በህብረት የማይወጣው የኢኮነሚ ችግር የለውም ብቻ ሳይሆን በኢኮነሚ ውስጥ ትልቅ የተጽኖ ተሳትፎ እንዲኖራቸው መንገድ ከፋች የሚያደርግ እና ሀገራቸውንም በኢኮኖሚ ውስጥ የተጽኖ ፈጣሪ ሚናዋ የላቀ የሚያደርጋት ነው፡፡ ይህ አይነቱ ህብረተሰቡም ሆነ የሀገሪቷ ህዝቦች በኢኮነሚ እራሳቸውን ከመቻል አልፈው ሀገራቸው ባለችበት ሀጉርም ይሁን በአለም ተጽኖ ፈጣሪ እንድቶን ያደርጋል፡፡
በአጭር ጊዜ ብድር
ተመጣጣኝ ወርሃዊ ክፍያ
የብድር ወለድ ምጣኔ
መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ
አብሮ ሰው ለመሆን ቅን ልቦች ያስፈልጋሉ፣ አብሮነትን የሚያጠናክር ተመሳሳይ ራዕይ እና አለማዎች ለግብ ያደርሳሉ፣ አብሮነትም ለጋራ እድገት ፈር ቀዳጅ ከመሆኑም ባሻገር የአንድነት ቃል ኪዳን በጎኅ ከአድማስ ባሻገር ስላለው ግብ አብሮ ይጓዛል ኑ በጎኅ አብረን እንጓዝ ጥሪዬ ነው።
የትምህርትና ስልጠና ኮሚቴ ሰብሳቢ
የስኬት ሚስጥሩ ከተናጥል ጥረት ይልቅ በትብብርና በጋራ መስራት ነው። ጎኅ ይህን የተረዱ ብርቱ
ሰዎች የተሰባሰቡበት የቁጠባና ብድር ማኅበር ነው። እርስዎም ይህን ማኅበር ተቀላቅለው አብረውን
እንዲያድጉ መልዕክቴ ነው!
ም/ሥራ አስኪያጅ በለው
ጎኅ፣ የአንድነታችንና የእድገታችን መሰረት ነው።
የትምህርት እና ስልጠና ኮሚቴ
"ህበረት" የዕድገት አስፈላጊ መሰረታዊ ቅንጣት ነው። ህብረት በአሰራር መንገድ/ሂደት (ሲስተመ) ሲደገፍ አዎንታዊ የምጣኔ ሀብት እድገትን ማረጋገጥ ይቻላል። ይምጡ በጋራ የገንዘብ እጥረትዎን እንፍታ።
ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ኀ/ሥ/ማ
የጋራ ተጠቃሚነትን እውን ለማድረግ፣
ሁኔታውን በተረዱ ባለ ራዕይ ወጣቶች የተመሠረተ የገንዘብ ተቋም ነው። እናንተም ይህን መልካም እድል
ተጠቅማችሁ ራእያችሁ እዉን የሚሆንበትን ተቋም እንዲቀላቀሉ ጥሪ ስናቀርብልዎት ከፍተኛ ኩራት
ይሰማናል።
ገንዘብ ያዢ
የምስራች!
ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ.የተ. የህብረት ስራ ማህበር የምስራች ነው።
የሰማችሁ እንኳን ደስ አላቺሁ ላልሰሙ አሰሙ።
የትምህርትና ስልጠና ኮሚቴ
የስኬት ጉዞ እርምጃ አንድ ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ.የተ. የህብረት ስራ ማህበር።
ህልምዎ ተሳክቶ ማየት ይፈልጋሉ? ኑ አብረን እንስራ አብረን እንደግ።
የብድር ኮሚቴ ሰብሳቢ
ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ.የተ. የህብረት ስራ ማህበር ከተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ
ከአባላቶቹ የሠበሠበውን ገንዘብ ለአባላቱ የተለያዩ ብድሮችን እየጠሰ ይገኛል። እርስዎም አባል ይሁኑ
ይቆጥቡ ፣ ይበደሩ ሀብት ያፍሩ ህልምዎን ያሣኩ እንዲሁም በዙሪያዎ ያሉትን አብረው ተደጋግፈው
ከምኞታቸው እንዲደርሱ ከጎንዎ ነኝ ይላል ጎኅ።
የብድር ኮሚቴ ፀሐፊ
ጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የሕ/ሥራ ማህበር ጊዜን በዋጅ መልኩ ከተመሰረተበት አመት ጀምሮ
ዘርፈ ብዙ የቁጠባና ብድር አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል። በመሆኑም በጎኅ የገንዘብ ቁጠባና ብድር
ይቆጥቡ ለቁም ነገር ይበደሩ ፣ ቁጠባን ባህላችን እናድርግ እያለ በደሰታ ይገልፃል።